በአማዞን ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት

ሮቦት የሠራተኛ ፎቶግራፍ ሲመርጥ
አጭር የምስል መግለጫወደፊት ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ሠራተኞችን ያባርር ይሆን?

ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ ይነጥቃሉ ተብሎ መወራት ከጀመረ ከራረመ። አሁን ተራ ወዛደር ብቻ ሳእሆን የሰው ኃእል አስተዳደር ሆኖም መግቢኣ መውጫ ሰዓትን ይቆጣጠራል፤ በሥራ ላይ ያለዎትን አፈፃፀም ይከታተላል። ይሾማል ይሸልማል፤ ካልሆነ ያባርራል።

ይህ ጉዳይ ተግባራዊ ጉዳዩ መገናኛ ብዙኃን ጆሮ የደረሰው ደግሞ አማዞን ውስጥ ነው። ግዙፉ የአማዞን ድርጅት ውስጥ ካሰቡት በተለየ ሁኔታ ሠራተኞችን በማባረር የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ውሏል ይላል ዘገባው።

ዘ ቨርጅ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ዘጋቢ እንዳስነበበው አማዞን ውስጥ ኮምፒውተሮች የሰራተኞችን ውጤታማነት እየመዘኑ እስከማባረር ደርሰዋል።

አማዞን በዝቅተኛ ክፍያና ከባድ የስራ ጫና ምክንያት በተደጋጋሚ ከሠራተኞች ቅሬታ የቀረበበት ሲሆን አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ የሚመለከተን እንደ “ሮቦት” ነው ሲል ምሬቱን ገልጿል።

ዘ ቨርጅ እንደዘገበው ብዙ ሠራተኞች በየዓመቱ እቃዎችን በፍጥነት ማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ከሥራቸው ይባረራሉ።

ይህ ሁኔታ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎች አለቃ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል የሚሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አሉ። ቴክኖሎጂው የሰዎችን ውጤታማነት ተከታትሎና መዝኖ ማስጠንቀቂያ መስጠት እስከመቻል ደርሷል። በሂደቱም ሁለተኛ እድል መጠየቅ እንደሚቻል ዘ ቨርጅ በዘገባው ላይ አመልክቷል።

በሮቦቶች እንደ ሮቦት መታየት

በንግድ ሥራዎች ላይ የህግ ባለሙያ የሆኑት ስታንሲ ሚቼል “አማዞን ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች በሮቦቶች እንደ ሮቦት ነው የሚታዩት” ይላሉ። ሠራተኞቹ እንዲያሳኩ የሚጠበቅባቸው የሥራ መጠንም ሆነ የውጤታማነት መለኪያዎቹ በውል አይታወቅም ሲሉም ያክላሉ።

አማዞን ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ “ሠራተኞች በኮምፒውር ውሳኔ ይባረራሉ የሚባለው ወሬ ፍፁም ውሸት ነው። እንደማንኛውም ድርጅት ለሠራተኞቻችን የሥራ ውጤታማነት መመዘኛ መንገድ ያለን ሲሆን ማንንም ግን ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ እገዛ ሳናደርግ አናባርርም። በፍጥነት የሚያድግ ድርጅት ስላለን በዘላቂ የሙያ ድጋፍ የሠራተኞቻችንን ብቃት ለማሻሻል እንተጋለን” ብሏል።

ድርጅቱ ምን ያህል በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እንደተደገፈና ሠራተኞችን ለማባረር እየተጠቀመ እንደሆነ በግልፅ አልገለፀም። read more from official

1 thought on “በአማዞን ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት”

  1. Белорусский трикотаж Свитмода|Молодежная женская одежда Свитмода|Одежда женская больших размеров Свитмода Бай|

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *